አንድነታችንን እናጠናክር! Amharic

*_ጥሪ_*

 አንድነታችንን እናጠናክር!
ጠላታችን የሆነውን ፍሽዝምን ለመቆጣጠር ወይንም ለመከልከል ሁላችንም በአንድነት እንቁም::
      አሁን ግዜ የለንም ነገር ግን ግዜ መምረጥ አለብን ምክንያቱም ትብብር ያስፈልጋል::
ራስን ለመከልከልና ትብብር ለማድረግ ጥሪ እናድርግ::
በሳክሶኒና ከዚህም  በአለፈ ሁላችንም ራሳችን መከላከል ግዴታችንን ነው::
አንድ ነገር ለመስራት በፓርቲ መደራጀት አይጠይቅም ግልፅ አላማ ይዘን ሁላችንም በአንድነት በመቆም  በአሁኑ ሰአት
የሚደርሰውን ሁኔታ በመገነዘብና ጥልቅ ግንዛቤ በማድረግና የአንድ ሰው የመኖርና የአለመኖር ግንዛቤ በማስጨበጥ
ራሳችንና የተጎዱ ወገኖችን  መርዳት:: አሁን ሁላችንንም እዚህ ሳክሶኒ አለን በቀጣይ በሁሉም ቦታ እንገኛለን::
አሁንም ነገም ከነገ ወዲያም አብረናችሁ አለን
ይህን የፓለቲካ ውስብስብና ቀውስ ሊያመጣ የሚችልን ነገር እንደ አላማ በመያዝ ቦርደሮችን በመዝጋትና ህገወጥ
አስተላላፊዎችን በመንግሥት ድጋፍ ተደርጎላቸዉ የዜጎችን መብትና ነፃነት ከመጋፍት አልፍ የዜጎች የመኖር ዋስትናን
የገፈፈ ስለሆነ ሁላችንም በአንድነት በመተባበርና በመተጋገዝ ይህን አስከፊና አሳፍሪ አላማ በአንድነት መከላከል
አለብን: ይህ ድርጊት በተለይ በሳክሶኒ ተባብሶ ይገኛል::
        ችግሩ ስደትን መቃወም አይደለም::
ሁላችንም እንደምንረዳው ይስደት ችግር ሳይሆን ጥላቻን ቂምን ብሎም ራስን ከፍ አድርጎ በማየት የተፈጠረ ክስተት ነው::
ዛሬ በሳክሶኒ ጀርመን ውስጥ የሚታየው እጅግ የከፍና ጥላቻውም በዚህ የማያቆም ነገ ከነገ ወዲያ በመላው ጀርመን
ብሎም በመላው አውሮፓ  እያቆጠቆጠ የመጣው የጥላቻ መንፈስ አሳፍሪነቱ  በገሀድ መታየት ጀምሯል:: 
ለምሳሌ በሳክሶኒ አካባቢ ስደተኞች በማታ ብቻቸውን በነፃነት መዘዋወርና ሀሳባቸውን  መግለፅ የማይችሉበት ደረጃ ላይ
ደርሰዋል::
በሳክሶኒ የሚታየው ችግር በጣም ከባድና ወደፊትም ይህ ጥላቻ እየጨመረ ሄዶ ወደ ከፍተኛ የህዝቦች ጠብ እያመራ ሲሆን
በተለይ AfD’S በህብረተሰቡ ሊያጠነክሩ የሚችሉትን መዋቅሮች እንዳይጎለብቱ አጥብቆ ሲከላከል ስለቆየ በህበረተሰቡ
ውስጥ ያሉትን መጠራጠሮች እንዲሰፍና እንዲጎለብት አስተዋፃ አድርጋል::
ይህ ሁሉ ችግርሲፈፀም  CDU መንግስት በቸልተኝነትና በምንቸገረኝነት ጉዳዩን ሲመለከት ቆይቷል:: 
አሮጌዎች የቀኝ አክራሪዎችና አዲስ የቀኝ ክንፍ አክራሪዎች  ለዜጎች የተጨነቁ አይመስሉም እንዲያውም ፍርሀትና
ጭንቀት በስደተኞች ላይ ጥለዋል:: ከዚያም አልፍ  መምታት : መግደል በመጨመር ላይ ይገኛል::ጥላቻውም የሚመነጨው
እኛ የተለየን በማለት ነው :: እርግጥ ነው የስው ልጅ ሁሉ አንድ አይነት አይደለም በመልክም በአስተሳሰብ በባህል
በሀይማኖት   በመሳሰሉትይለያያል ቢሆንም ግን አንዱ አንዱን አይበልጥም ::
በዚህ በግሎባሊዜሽን ዘመን እኔ ምርጥ ዜጋ ነኝ ብሎ አንድ የሆነውን የሰው ፍጡር አሳንሶ ማየት  እጅግ ኃላቀርነትና
የሀሳብ ደካማነትን ያሳያል በአሁኑ ሰአት በብዙ አውሮፓ አገሮች የቀኝ አክራሪዎችና የናዚ ደጋፊዎች እያቆጠቆጡና
እጨመሩ  በመምጣት ላይ ይገኛሉ ይህ ደግሞ አንዳንድ የመንግሥት ሀላፊዎችና ፖለቲከኞች እና ይግል ባለሀብቶች
 ሁኔታወችን በማመቻቸትና  በመደገፍ የበለጠ እንዲስፍፍ ምቹ ሁኔታወችን ፈጥረዋል::
ዛሬ በሚዲትራኒያን የምናየው ከፍተኛ የሆነ የሰባው ቀውስ አንዱ የዚህ የፖለቲከኞችና የሞኖፖሊስቶች ዋና አላማ ሆኖ
በግልፅ ይታያል::
     ራስህን መከላከል መምረጥ አለብህ!
ዛሬ የቀኝ ክንፍ አክራሪዎች የበላይነትን ለመያዝ  እያመጠት ያለው የጥላቻና የበላይነት መንፈስ  ከማቆጥቆጥ አልፎ
በመሬት ላይ በተግባር በመስፍፍትና በመፈፀም በተለይ መጢ ተብለው በሚፈረጁት ላይ ለጥቃቱ ሰለባ ሲሆኑ ይታያል
::ስለዚህ ሁላችንም በአንድ ላይ በመተባበር እነዚህን የቀኝ ክንፍ አክራሪዎች መጋፈጥ ካልቻልን ነገ ከነገ ወዲያ
የሚያስከትሉት ማህበራዊ ቀውስ ይህ ነው የማይባልና  በዚህ ጀነሪሽን የማይመጥን ስለሚሆን ሁላችንም አበክረን
በአንድነት በመቆም ልንከላከለው ይገባል::
ሰወች ልዩነታችን እንዳለ ሆኖ በመከባበር አብረን ስኖር  ውብ የሆነችና ሰላማው አለምን መፍጠር እንችላለን ይህ
ሳይሆን ቀርቶ ግን መከባበርና ልዩነታችንንየማንረዳ ከሆነ አለማችን አስጠይና አስከፊ ሆና እናገኛታለን: ስለዚህ
ሁላችንም በአገኘነው መንገድ ሁሉ ይህን ክፍ የጥላቻ መንፈስ የተጠናወታቸውን ዜጎች በማረቅና በማስተማር ግዴታችንን
እንወጣ ::
ስለዚህ ነገ ዛሬ ሳንል በተለያየ መንገድ በማስተማርና በማነፅ ከክፍ ድርጊታቸው ለመታገል ሁላችንም ቆርጠን እንንሳ::
        *_ጥሪን ይመለከታል!!_*

-በነሀሴ 24/2019 በዲሪስደን አገር አቀፍ  ሰላማው ሰልፍ ይከሀዳል
   የሰላማው ሰልፍውአላማ አንድነታችንን በማጠናከር ጥላቻንና የዘር የበላይነትን መቃወም
-ህዳር 1 እና 3 /2019 በቸሚኒቲስ ሰላማው ድምፅ ይሰማል 
  አላማው የስደተኞች ድምፅ ጎልቶ ይሰማል 
– በአጠቃላይ ለዚህ ሰላማው ሰልፍ ሙሉን ድጋፍ ከምስራቅ ጀርመን ይደረጋል :: እናንተምየራሳችሁንአስተዎፆ አድርጉ::
– ለዚህ ፀር ጥላቻ  በተለይ ፀረ ስደተኞች ይዘው የሚንቅሳቀሱትን ለመዋጋት ሁላችንም በአንድ ላይ ሆነን እንዋጋቸው
 በተለይ ወደ ተለያየ ካንፖች በመሄድና የተለያዩ መንገዶችን በመጠቀም  ለነሀሴ24/2019  ሳክስኒ ለሚደረገው
ሰላማው ሰልፍ የትራንስፖርትና የመሳሰሉትን አቅርቦቶች እንድታሟሉ እንጠይቃለን::
 እንደዚሁም የተለያዬ የኒት ወርክ መንገዶችን በመጠቀም ራስን ማጎልበትና ማጠንከር ::
-ሀምሌ 28/2019በዲሪስደን አገር አቀፍ ስብሰባ ይካሄዳል
  አላማው  ተጨባጭ እቅድ ማውጣትና የወደፊት አካሄዳችን ምን መምሰል  እንዳለባት ውይይት ይደረጋል::
   Welcome united